Tuesday, 16 June 2015


                  ጥንዶች የሞሉዋቸው የማጥኛ ክፍሎች 
በ ቤዛዊት ተፈሪ(መቀሌ ዩንቨርሰቲ)
በ ጥንዶች የሚሞሉት የመማሪያና የማጥኛ ክፍሎች(ኒው ቢዩልዲንግ)







ኡኡኡ........ኧረ በየት በኩል እናንብብ እሺ ? ይህ ጩኽት ከየትም የመጣ አይደለም ከዚሁ ከግቢያችን ተማሪዎች ሰሞኑን መሰማት  የጀመረ ድምፅ ነው።

  (ማለት ፈተና በሚደርስበት ሰአት ደሞ ሁሌም ከፍ ብሎ ይሰማል )ፈተና ሲደርስ  አብዛኛው ተማሪ በደንብ  ያጠናል፣ ላይብረሪ ይሞላል ስለዚህ ያለው አማራጭ ባዶ ክፍሎችን (ስፔስ) መጠቀም ነው። እሱስ ሲጠፋ የት ይኬድ ?
          
 ለሶስት ተከታታይ ቀናት ስፔሶች ላይ ጥናት ለማድረግ አንደሞከርኩት ከሆነ በአማካይ 5 ክፍሎች 3ቱን  ጥንዶች  የፍቅር አክርማቸውን ሲቀነጥሱባቸው ያመሻሉ (ይህ ቁጥር እንደየጊዜው ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል) በተለይ በዚ ቀውጢ በፈተና በተጨናነቀ ሰአት ደሞ እነዚህ  ክፍሎች ፈላጊያቸው በጣም ይበዛል

ይህን የቁጥር መረጃ ያገኘሁት ማታ ነው ነገር ግን በቀንም ስፔስ የሚጠቀሙ ተማሪዎች የሉም ማለት አይደለም። ይህ ድርጊት የጥናት ስርአቱን ከማስተጓጎል ባለፈ በራሳቸው (በጥንዶቹ) ላይም አደጋ ሊያስከትል ይችላል
          
 ስለ ጉዳዩ አጋር የጥበቃ ሰራተኞችን አነጋግሬም ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ እንደደረሰ እነሱ ግን በተቻለ አቅመ ሁሉ ጥበቃ ለማድረግ እየጣሩ እንደሆነ እንዲሁም በተወሰነ ሰአተ ልዩነት በክላሶቹ ውስጥ አሰሳ እንደሚያካሂዱ ተናግረል

No comments:

Post a Comment