Tuesday, 16 June 2015


            4 ቀን ልጅ የሽንት ቤት ቱቦ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ



ቤዛዊት ተፈሪ (መቀሌ ዩንቨርስቲ)
ህፃኑ  ልጅ ተጥሎ የተገኘበት የሽንት ቤት ቱቦ (ብሎክ ስድስት ጀርባ)


በመቀሌ ዩንቨርሲቲ በአድ ሀቂ በሴቶች መኖሪያ አካባቢ ከተወለደ 4ቀን የሞላው ጨቅላ የሽንት ቤት ቱቦ ውስጥ ተጥሎ ተገኝቷል። ህፃኑ ሊገኝ የቻለው የሽንት ቤት መስመር በመበላሸቱ ምክንያት የሚመለከታቸው አካላት ቱቦውን ሊያስተካክሉ  በከፈቱበት ሰአት ነው።

ከዚያም እንግዳ ነገር ሲያስተውሉ ለተማሪዎች ህብረት እንዲሁም ለመቀሌ ከተማፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታውቀው ህፃኑን ከተጣለበት ጉድጓድ ህይወቱ አልፎ ሊወጣ ችሏል። የተማሪዎች ህብረት ፅህፈት ቤትም ተማሪዋን ለማግኘት ከባድ ጥረት ካረገ ቦሃላ ልጅቷ እራስዋን ለህግ አሳልፋ ሰታለች

ተማሪዋ የሶስተኛ አመት የሲቪክስ ተምህርት ክፍል ተማሪ ስትሆን ልጁንም ትምህርት ከመጀመሩ በፊት እንዳረገዘችው ታውቋል። ለተለያዩ ሰዎችም ይሆድ ህመም ነው ትል ነበር።

 በአሁኑ ሰአት ተማሪዋ ለሰችው ወነጀለ በፈረድ ቤት ቁጥጥር ስር ትገኛለች።   በአሁኑ ሰአት ማረሚያ ቤት ትገኛለች ።ህፃኑ በተገኘበት ሰአት በቦታው ላይ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንት ተገኝቶ ነበር።



No comments:

Post a Comment