Tuesday, 16 June 2015


የተማሪዎች የስነ ምግባር ጉድለት ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተነገረ 
በ ቤዛዊት ተፈሪ(መቀሌ ዩንቨርስቲ)

ፊትለፊት ለ ፊትለፊት ያሉት የወንዶችና የሴቶች መኖሪያ ህንፃ( ብሎክ ዘጠኝ እና አስር)



በመቀሌ ዩንቨርስቲ አድ ሀቂ ካምፓስ ውስጥ የሚኖሩ ሴት ተማሪዎች ዶርም አካባቢ ከወንዶች የሚሰነዘሩ አፀያፊ ቃላት ዶርም አካባቢ ያላቸውን  እንቅስቃሴ ከባድ እያደረገባቸው እንደሆነ ገለፁ።

  ሂስትሪ / ክፍል ተማሪ የሆነችው ተማሪ አለም አቦሰጥ እንዲህ ትለናለች" ሁሌም ወደ ዶርም በምንገባበት ጊዜ እናቱ፣ ቆንጅዬ፣ ኧረ ሰላም በይን፣ ምን ይዘጋሻል፣ ይድፋሽ የሚሉ የትኮሳ ቃላቶች ይወርዱብናል  ይሄ እንደውም ትነሽ ነው ከበድ ያለ ስድብም ሊሳደቡ የችላሉ" ትላለች።

 ተማሪዎች እንደሚሉትም ይህ ነገር እንደ ትንሽ መቆጠር የለበትም በሴቶቹ ላም የሚያደርሰው ስነ ልቦናዊ ተፅእኖ ቀላል አደለምና

 
ለዚህም ዋናው ምክንያት የሚሉት የወንዶችና የሴቶች ዶርም ፊት ፊት መሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል። ተማሪዎች ይህን ጉዳይ በተደጋጋሚ ለፕሮክተር ቢያሳውቁም ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት አልተቻለም። ለዚህም ዋናው ችግር የብሎኮቹ አሰራር እንደሆነ ይነገራል።


No comments:

Post a Comment